Thursday, June 25, 2020

ኢትዮጵያ ሃገረ ምስጢር !


ሠላም ለሁላችሁ ይኹን!

ግንቦት 13 ቀን 2012 ዓ.ም

ዉድ ቤተሰቦቼ በጸሎት እየበረታችሁ እንደሆነ አልተጠራጠርኩም፤ ፈጣሪያችን ያበርታን !

ከዳዊት መዝሙር የሚበልጥ ጸሎት እንደሌለ ተማምረናል ፤ የዛሬዋን እንሆ!
ጠዋት ስንነሳ ለጸሎት ሥንቆም ከዘወትር ጸሎታችን ቅድሚያ እነዚህ የዳዊት መዝሙራት ይጸለያሉ መዝሙር 5 ፤ 56፤ 62 
ማታ ከመተኛታችን በፊትም የሰላም ሌሊት እንዲያደርግልን ከመጸለያችን በፊት መዝሙር 140 ይጸለያል ፤
(ምስጢሩም ጠዋት 3 ማታ 1 ይሆናል)
የዛሬዉ ሁለተኛዉ መልዕክቴ በምሥጢር ስለተመላችዉ ስለ ሃገራችን ኢትዮጵያ ይሆናል !
ኢትዮጵያ ሃገራችንን  ወደ ቀደመ ክብሯ እና ለዛዋ ይመልስልን !
ማንኛዉም መፍትሔ ያለዉ ከቤተክርስቲያናችን መሆኑን የቀደሙ ነገስታት ጠንቅቀዉ ያዉቃሉ ፤ ስለሆነም ምክር ይጠይቋታል እርሷም ትሰጣቸዋለች፤ መፍትሔዉም ከእግዚአብሔር ተቀብላ ስለሰጠቻቸዉ ያማረ የሰመረ ነበር፤ አሁንም ፓርላማዉ ያለ እርሷ የሚያዋጣ አይሆንም፤ እንዲህ ሕዝቡን የሚያፋጀዉ ቤተ ክርስቲያንን በማስወገዳችን ነዉ፤ ሕጉን ከዳሰሰችዉ የቀና ይሆናል ፤ አሁንም ትግባና ታስተካክለዉ ፤ ቀብታ ያነገሰቻቸዉ ነገስታትን ጸሎት በእንተ ንጉሥ ብላ ትጸልይላቸዉ ነበር፤ አሁን ግን ይኽ ጸሎት ቢኖርም ንጉሱ የለም፤ ቅብዓ-ነገሥቱም ቀርቷል፤ የቅብዓ-ነገሥቱ ብልቃጥ ግምጃ ቤት ተቀምጦ ይጮኻል ! ! !
የነገሥታት አምላካቸዉ ወደ ነበረን ክብራችን ይመልሰን ፤ አሜን + + +

No comments:

Post a Comment