ሰላም ለኩልክሙ !
ሀ. ነገደ ኦሪት
ለ. ነገደ ካም
ሐ. ነገደ ሴም
መ. ነገደ እስራኤል
ለ. ነገደ ካም ሦስት ነገዶች ሲሆኑ ነገደ ሻንቅላ ፣ ነገደ ቅማንት፣ ነገደ ወይጦ እና ነገደ ሽናሻ ናቸዉ ፤ ሁሉም የካም ልጅ ከነዓን ልጆች ናቸዉ፡፡ የቅማንቶች አባት አይነር የካም ልጅ የከነዓን የልጅ ልጅ ነዉ፡፡ሚስቱ እንተላ ትባላለች፡፡
ሐ. ነገደ ሴም (ነገደ ዮቅጣን) ፤ ሴም 15 ልጆችን ወለደ 3ኛዉ አርፋክስድ ይባላል፤ አርፋክስድ ዓቦር ፋሌክንና ዮቅጣንን ወለደ፣ ዮቅጣን 13 ልጆችን ወለደ አንዱ ሳባ ነዉ፤ የሳባ የልጅ ልጁ ኢትዮጲስ ይባላል ከኢትዮጲስ ኢትዮጵያ ተባለች፤
ኢትዮጲስ 5 ልጆችን ወለደ ፤ እነሱም ፡
1. ላክንዱ -
2. ሳባ - ትግሬዎች
3. ኖባ - ጎጃም ነጭ አባይ እና ጥቁር ዓባይ ያለበት
4. በለዉ - ሰግላና ሐማሴን ኤርትራዉያን
5. ከለዉ - አማራ ወልቃይት ጠገዴ
የኢትዮጵያ ዋና ባላባቶች 6 ናቸዉ ፤ አማራ (ወልቃይት ጠገዴ ጎጃም ጎንደር ሸዋ) ፣ ትግሬ ፣ አገዉ ፣ በደዉ ፣ አስገዴ ብቅላ ፣ ሐባብ ናቸዉ
በደዉ(ኤርትራ የሚገኙ ብሌኖች) ፣ አስገዴ ብቅላ(ሐረር ድሬዳዋ የሚገኙ) እና ሐባብ(አፋር እና ሱማሌ የሚገኙ) ከወንድሞቻቸዉ ተለይተዉ በእስልምና ሃይማኖት ገብተዉ ልዩ ወገኖች ሆነዋል ፤ ሌላዉ ሕዝብ ከእነዚህ ሲዋለድ የተገኜ ነዉ፡፡
መ. ነገደ እስራኤል ከቀዳማዊ ሚኒሊክ ጋር ታቦተ ጽዮንን ጽላተ ሙሴን አጅበዉ የመጡ ሲሆን በብዛት በጎንደር አካባቢ የሚኖሩ እና ከሌሎቹ ነገዶች በተለየ ፈላሲ(ፈላሻ) የተሰደዱ በመባል ይታወቃሉ፤ በእደ ጥበብ እና ቅርሳቅርስ ስራዎች የታወቁ የተደነቁ ናቸዉ፡፡
በ327 ዓ.ም በአጼ ዐምደ ጽዮን ዘመነ መንግስት በትግሬ ጉርዓ ከሚባል ኣገር ከኩሎ ግዛይ ክፍል የወጣ ሠራዊት ከአዝማች ስብሓት ጋር መጥቶ በአይመለል ተሠራ፡፡ ስለዚያም ያ ኣገር እና ሕዝብ ጉርዓጌ ተባለ፡፡
በኢትዮጵያ የገቡ እስላሞች 4 ዓይነት ናቸዉ፤ 1ኛ ፡ ሕምሪያ (ቀይ) ፣ 2ኛ ፡ ትግሬ(ነጋዴ) ፣ 3ኛ፡ አርጎቦች 4ኛ፡ በመሃመድ ጊዜ ተሰደዉ የመጡት ናቸዉ፡፡
ምንጭ ፡ አለቃ ታዬ የኢትዮጵያ ታሪክ ፣ ክብረ ነገስት ገጽ 40 እስከ 50 ፣ ኤር 38፡7 ፤መዝ 68፡30 ዘፍ 9፡18 ሐዋ 8፡36 ሶፎ 3፡10
No comments:
Post a Comment