Thursday, June 25, 2020

ንግባኬ ሃበ ጥንተ ነገር !

ሠናይ ለክሙ !
ሰኑይ ሰኔ 15 ቀን 2012 ዓ.ም

ንግባኬ ኀበ ጥንተ ነገር !
ወደ ቀደመዉ ነገራችን እንመለስ !
Let’s get back to the ancient times!

በዉኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዥጉርጉርነቱን ይለዉጥ ዘንድ ይችላልን? በዚያን ጊዜ ክፋትን የለመዳችሁ እናንተ ደግሞ በጎ ለማድረግ ትችላላችሁ፡፡   ኤር. 13፡23

Can the Ethiopian change his skin or the leopard his spots? May ye also do good, that are accustomed to do evil. Jeremiha 13: 23

የፀሐይ ግርዶሽ በተለየ መልኩ ለምን ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ላይ ታየ ብለን ለመመርመር ኢትዮጵያዊ መሆንን ይጠይቃል፤ ለምን ንጉስ ላሊበላ ያችን ቦታ መረጦ አባያተ ክርስቲያናትን አነጸ፤ ቦታዉ ምን አለዉ፤ እንዴት ከፀሐይ እና ጨረቃ ጋር ተዛመደ ለማለትም ይኽን አሁን ያለንን ልፍስፍስነት እና የፈረንጅ ቀላዋጭነታችን ስንተዉ ያኔ ይገለጽልናል!
የንግሥና ስርዓት ከንጉሣችን አባባ ጃንሆይ የተቆረጠዉ ገመድ ይቀጠልና እንጓዝ ብለኽ አንዱን ወጣት ስትጠይቀዉ እንዲኽ ይልሃል….
በዋናነት ብሎ ንግግሩን ይጀምራል  የዉስጡን ባዶነት ለመሸፈን ……  ከዚያ አይን አይኑን ስታየዉ ምንም የለዉም፤ እርሱ ግን ለራሱ ሊቅ ነዉ፤ ሲናገር የቆየዉን ነገር እንደገና ይደግምልሃል፤ እንዴት በዚህ ዘመን እንደገና ወደኋላ እንጓዛለን ፤ አሁን እኮ ያለነዉ የቴክኖሎጂ ዘመን ላይ ነዉ ይልሃል በጣም በመኩራራት ፤ እንዴ ብሎ ይጨምርልሃል …..
አሁን በዚች ትንሽ የሃሳብ ሳጥን ዉስጥ ነዉ ያለነዉ ፤ ሚዲያ የምንላቸዉ ከቴሌቪዥን እስከ ሬዲዮ አንድ ቁምነገር እንኳን ካወሩ በጣም ደስ ይለኝ ነበር፤ እንደማያወሩ ማረጋገጫዉ ቴሊቪዥንም ሬዲዮም ጣቢያቸዉ(ቻናል) ብዙ ነዉ፤ ስትቀይር ብትዉል ወይ አንዲት ከአንጀት የሚገባ፤ ታዲያ አንድ ሬዲዮና አንድ ቴሌቪዥን ጣቢያ የነበረን ጊዜ ለምን ይሆን እንዲያ ማፍጠጣችን ፤ ስላልሰለጠንን እንደምትለኝ ቀድሜ አወቅሁት፤
ዛሬም ጥሩ አደርገዉ በአኗኗራቸዉ ያጠመቁን አዉሮፓ እና አሜሪካ እኛን እያዩ እንዴት ስኬታቸዉን እንደሚያጣጥሙ እያወቅን ዛሬም የእነሱ አድናቂዎች ነን፤ ሚዲያዎቻችን ዙሮዙሮ ወቅን(እዚያዉ) ብያቼዋለሁ ፤ የእዉቀታቸዉ መለኪያ የስፖርት ዘገባ ብቻ ነዉ!

የባሕል ልብሳችን ትዝ የሚለን ኳስ ሜዳ ወይም ስራና መዝናኛ ቦታ ስንሔድ ሳይሆን በዓል ሲመጣ ነዉ፤ ታዲያ ሃገሬ ኢትዮጵያ የሚለዉ ዘፈን ሲሰማ አጨባጫቢዎች ነን፤
ፖለቲከኛዉ እዉቀቱ ምንም ስለሆነ ንግግር የሚጀምረዉ የቀድሞዉን የአባቶቻችን ስርዓት በመንቀፍ በማንቋሸሽ ነዉ፤ ታዲያ ምኑ ላይ ነዉ እዉቀቱ፤ ከዛሬዉ አዋቂ ተብየ ፈጥኖ ከሚደሰኩር ፕሮፌሰር እኮ የቀድሞዉ ታፍ የማይቀማዉ ገበሬ የማይደግመዉን ነገር በአጫሩ ጣል ሲያደርጋት ቤት ትሰራለች፤
 ግድ የለም እንሸነፍ አባቶቻችን በንጽሕናም፤በእዉቀትም፤በሃሳብም፤አገር በመምራትም ይበልጡናል፤ እነሱን ለመምሰል ጉዞአችንን አንድ እንበል፤ ንግባኬ ኀበ ጥንተ ነገር - ወደ ቀደመዉ ግብራችን እንመለስ ፤ ያኔ ፈጣሪ ያግዘናል ፤ እንደ ትናንትናዋ ጠፍታ(ተጋርዳ) እንደተገለጸችዉ ፀሐይ የጠፋችዉ ኢትዮጵያ ትገኛለች !

አምላከ ላሊበላ አምላከ ቴዎድሮስ አምላከ ምኒልክ አምላከ ኃይለ ሥላሴ ከተኛንበት ይቀስቅሰን ፤ ንጉሥ ከመንበሩ ጳጳስ ከደብሩ አይንሳን ፤ አሜን + + +

No comments:

Post a Comment